ኔልሰን ማንዴላ፣ የደቡብ አፍሪካን የዘር መድልዎ ሥርዐት ሲታገሉ፣ 27 ዓመታትን በእስር ያሳለፉና በመጨረሻም የአገራቸው የመጀመሪያ ጥቁር ፕሬዚዳንት ለመኾን የበቁ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም ታላቅ ምሳሌ ኾነው ያለፉ ሰው ነበሩ።
ኬት ባርትሌት ባደረሰችን ዘገባ እንደጠቆመችው፡ “ማንዴላ፥ ከኅልፈታቸው 10 ዓመታት በኋላ አገራቸው ያለችበትን የዛሬ ይዞታ ቢመለከቱ፣ በእጅጉ ያዝኑ ነበር፤” ሲሉ፣ የቀድሞ ጓዶቻቸው፣ የቤተሰባቸው አባላት እና ተንታኞች በአንድ ድምፅ ይናገራሉ።
ሙሉ ዘገባውን አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።