በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የሠራተኞች የደመወዝ ወለል ስምምነትን እንድታጸድቅ የሥራ ድርጅቱ ጠየቀ


ኢትዮጵያ የሠራተኞች የደመወዝ ወለል ስምምነትን እንድታጸድቅ የሥራ ድርጅቱ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00

ኢትዮጵያ፣ የሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስነውን ስምምነት እንድታጸድቅ፣ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት(ILO) ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፈደሬሽን ደግሞ፣ ሠራተኛው፥ “ለመቶ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎች” እንዳሉት አመልክቷል፡፡

የኮንፈዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የአገሪቱ ሠራተኞች ለረዥም ጊዜ ከሚያነሧቸው ጥያቄዎች አንዱ፣ የመደራጀት መብት መከበርን እንደሚመለከት ተናግረዋል፡፡ የሠራተኛው ክፍያም፣ በልቶ ለማደር እንደማይበቃ ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን፣ በመንግሥት ላይ ጫና እያደረግን ነው፤ ብለዋል፡፡

መንግሥት በበኩሉ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን ለመወሰን ጥናት እያደረገ እንደኾነ አስታውቋል፡፡

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንድ ባለሞያ ደግሞ፣ የሠራተኛው ክፍያ ዝቅተኛ መኾን፣ ሌሎች መብቶቹን እንዳይጠይቅ አድርጎታል፤ ይላሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG