በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ ሰባት ሰዎች በእሳት ተቃጥለው ተገደሉ


የጆሃንስበርግ ፖሊስ ወንጀል በሚበዛባት ዲፕስሉት ከተም በሥራ ላይ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)
የጆሃንስበርግ ፖሊስ ወንጀል በሚበዛባት ዲፕስሉት ከተም በሥራ ላይ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)

ተደጋጋሚ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 7 ሰዎች፣ እጅ-እግራቸውን ታሥረው፣ በእሳት ተቃጥለው መገደላቸውን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እና ነዋሪዎች አስታውቀዋል።

ከፍተኛ ወንጀል፣ ግድያ እና መደፈር እንደሚታይባት በሚነገረው ዲፕስሉት በተሰኘች እና ከጆሃንስበርግ በስተ ሰሜን በምትገኘው ከተማ የተፈጸመው ግድያ፣ በቡድን በመንጋ በመጡ ሰዎች ነው ተብሏል።

ዓርብ ምሽት ላይ በእሳት የተቃጠሉ ሰዎች እንደተገኙ ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ፣ ሁለት በእሳት የከሰሉ አስከሬኖችን ሲያገኝ፣ በማግስቱ ትናንት ቅዳሜ ደግሞ አምስት ተጨማሪ አስከሬኖች ተገኝተዋል።

ሟቾቹ ድብደባ ከደረሰባቸው በኋላ፣ በእሳት ተቃጥለው መገደላቸውን ቅድመ ምርመራዎች እንደሚያመለክቱ ፖሊስ ገልጿል።

ጎማ በአንገታቸው ላይ ጠልቆ እሳት እንደተለኮሰባችው አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

ስድሳ ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ደቡብ አፍሪካ፣ እየተጠናቀቀ ባለው የፈርጆች ዓመት በቀን 68 ግድያዎች እንደተፈጸሙ ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG