በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንባ ጠባቂ ተቋም በግሉ ዘርፍ አስተዳደራዊ በደሎች ላይ “ምርመራ ልጀምር ነው” አለ


እንባ ጠባቂ ተቋም በግሉ ዘርፍ አስተዳደራዊ በደሎች ላይ “ምርመራ ልጀምር ነው” አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በግሉ ዘርፍ የሚፈጸሙ አስተዳደራዊ በደሎችን መመርመር ሊጀምር እንደኾነ አስታወቀ።

የተቋሙ ዋና እንባ ጠባቂ ዶር. እንዳለ ኃይሌ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ከሳምንት በፊት በተወካዮች ምክር ቤት ተሻሽሎ በጸደቀው ዐዋጅ፣ ተቋማቸው፣ በግሉ ዘርፍ ያሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የመመርመር ሥልጣን እንደተሰጠው ተናግረዋል፡፡

በዚኽም መሠረት፣ መሥሪያ ቤታቸው፣ አቤቱታዎችን መቀበል እንደጀመረ ያስታወቁት ዶር. እንዳለ፣ “የምርመራ ሥራችን በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ ያተኩራል፤” ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጠው፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን በበኩሉ፣ በግሉ ዘርፍ ልዩ ልዩ የመብቶች ጥሰቶች እንደሚፈጸሙ ገልጾ፣ ለእንባ ጠባቂ ተቋሙ የተሰጠው ሥልጣን፣ ችግሩን ለመታገል እንደሚያስችል አመልክቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG