በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍትሕ ሚኒስቴር በዐማራ ክልል የታሰሩ የትግራይ ተወላጆችን እንዲያስፈታ ተጠየቀ


ፍትሕ ሚኒስቴር በዐማራ ክልል የታሰሩ የትግራይ ተወላጆችን እንዲያስፈታ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00

በፌዴራሉ መንግሥት በሽብርተኝነት ተፈርጆ ከነበረው ህወሓት ጋራ ግንኙነት አላችኹ ተብለው፣ ከሦስት ዓመት በፊት የተያዙ የትግራይ ተወላጆች፣ አሁንም በዐማራ ክልል እስር ቤቶች እንደሚገኙ፣ አንድ ኢትዮጵያዊ የመብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ፡፡

ሂዩማን ራይትስ ፈርስት የተባለው ይኸው ድርጅት፣ በሰሜንና በማእከላዊ ጎንደር ባሉ እስር ቤቶች፣ ከ100 በላይ የትግራይ ተወላጆች ታስረው እንደሚገኙ፣ “ባደረግኹት ክትትል አረጋግጫለኹ፤” ብሏል።

ምክትል ዲሬክተሩ አቶ መብርሂ ብርሀነ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የታሳሪዎቹ ክስ፣ በዐማራ ክልል እንዲታይ መደረጉ ሕጋዊ እንዳልኾነ ተችተዋል፤ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሠረት እንዲያስፈታቸውም ጠይቀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ የዐማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በበኩሉ፣ “ጉዳዩን አጣራለኹ፤” የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG