በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን አጋሮቿ የመካላከያ ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ጠየቀች


ዩክሬን አጋሮቿ የመካላከያ ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ጠየቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ፣ የሀገራቸው ጦር የሩሲያን ወረራ ለመመከት የሚያስፈልገውን የጦር መሣሪያ እንዲያገኝ ምዕራባውያን አጋሮች የመከላከያ ምርታቸውን እንዲያሳድጉ ጠየቁ።

ኩሌባ በብራሰልስ ከኔቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ሲናገሩ “ምዕራቡ ዓለም የማምረት አቅሙን ለማስፋት የፖለቲካ ፍላጎት ይጎድለዋል ብሎ ለማመን የሚያበቃ አንድም ምክንያት የለም፡፡ይሁን እንጂ ግን ያንን ግብ ለማሳካት መከናወን ያለባቸው ብዙ የቴክኒክ ስራዎች አሉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በጦርነቱ አደጋ ላይ ያለው የዩክሬን ደህንነት ብቻ ሳይሆን መላው የአውሮፓ አትላንቲክ አካባቢ ጸጥታ እና ደህንነት ጭምር ነው” ያሉት ኩሌባ “ዩክሬን የግዛት አንድነቷን የማረጋገጥ ግብ ላይ አተኩራ ትቆያለች፣ ይህን ከማድረግ ምንም የሚያግደን የለም" ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አያይዘውም "በዚሁ መቀጠል አለብን ትግላችንን መቀጠል አለብን "ዩክሬን ወደ ኋላ አትመለስም." ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኔቶ ዋና ጸሃፊ ዬንስ ስቶልተንበርግ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ሩሲያ በቻይና ላይ የበለጠ ጥገኛ እንድትሆን ኢኮኖሚያዊ ጫና እየገጠማት መሆኑን ጠቅሰው፣ ወታደራዊ ግፊቱም የሰሜን ኮሪያ እና የኢራን የጥይት እና የጦር መሣሪያ ድጋፍ ጥገኛ እንድትሆን እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

“ዩክሬናውያን በጦርነቱ ቀደም ብሎ በሩሲያ ተይዞ ከነበረው ግዛት 50 በመቶውን ግዛት መልሰው መቆጣጠራቸውብ የጠቀሱት የኔቶ ኃላፊው በሩሲያ ጦር ላይ የመሣሪያ እና የሰው ኃይል ኪሳራ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ግን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጦርነቱ ለመግፋት ቁርጠኝነታቸው እንዳለ በመሆኑ ሩሲያን አሳንሶ ማየት እንደማይገባ ኃላፊው አስጠንቅቀዋል፡፡

"የሩሲያ ኢኮኖሚ ጦርነቱን በመቀጠል ቁመና ላይ ነው" ያሉት ስቶልተንበርግ "ፑቲን በጦርነቱ በሰው ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች ያላቸው ትዕግሥት ከፍተኛ ነው፡፡ ሩሲያ ስለ ዩክሬን ያላት ዓላማም አልተለወጠም." ብለዋል፡፡

ስቶልተንበርግ አንዳንድ የኔቶ አጋሮች ኤፍ 16 (F-16) ተዋጊ ጄቶችን ወደ ዩክሬን ለመላክ ያደረጉትን ውሳኔ አወድሰው፣ አውሮፕላኖቹ የዩክሬን አየር መከላከያን በማጠናከር እና የሩስያን ኢላማዎች የመምታት አቅምን ለማጠናከር እንደሚረዱ ተናግረዋል ።

ይሁን እንጂ በጦር ሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ በመሠረታዊነት መለወጥ የሚችል አንድ ብቸኛ መንገድ እንደሌለ እና ሩሲያውያኑን ወደ ኋላ ለመግፋት የበርካታ ነገሮች ጥምረት እንደሚያስፈልግ ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል፡፡

ስቶልተንበርግ “አጋሮች ለረጅም እና ከባዱ ትግል መዘጋጀት አለባቸው” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG