በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባማን በመሣሉ ዝናው የናኘው ሠዓሊ ቡሩሹን ወደ አፍሪካ መሪዎች ጠቁሟል


ኦባማን በመሣሉ ዝናው የናኘው ሠዓሊ ቡሩሹን ወደ አፍሪካ መሪዎች ጠቁሟል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:52 0:00

አሜሪካዊው የጥበብ ሰው ኬህንዴ ዋይሊ፣ የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማንና የፖፕ ሙዚቃ ንጉሡን ማይክል ጃክሰንን ምስል በመሥራቱ ይታወቃል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ፣ ብሩሹን ወደ አፍሪካ በማዞር፣ 11 የቀድሞ እና የወቅቱን መሪዎች ምስል፣ ፓሪስ ከተማ ላይ ለእይታ አቅርቧል።

ኬህንዴ ዋይሊ፣ 11ዱን ፕሬዚዳንቶች የሣለው፣ በአውሮፓ ታሪካዊ የመሪዎችን አሣሣል መሠረት በማድረግና በዚያው መነጽር በማየት ነው።

ምስላቸው በሠዓሊው ከተሠራላቸው ውስጥ፣ የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ይገኙበታል።

የቪኦኤዋ ሊዛ ብራያንት፣ ዐውደ ርእዩን ጎብኝታ የላከችውን ዘገባ ነው እንግዱ ወልዴ ወደ ዐማርኛ መልሶታል።

XS
SM
MD
LG