በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻግኒ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ


ቻግኒ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:20 0:00

ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኬረሙ ወረዳ ባለፈው ዓመት ተፈናቅለው፣ በዐማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ቻግኒ ከተማ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ ሁለቱ፣ በረኀብ ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ ገለጹ።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት የሁለት ሕፃናት ሕይወት እንዳለፈ ያስታወቁት፣ የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ አቶ መሐመድ ሐሰን፣ ይህም፣ በአንድ ዓመት ውስጥ በረኀብ ሕይወታቸው ያለፉ ሕፃናትንና አዛውንቶችን አኀዝ 55 እንዳደረሰው ገልጸዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ፣ ከ2ሺሕ400 በላይ ብዛት እንዳላቸውና ባለፈው ዓመት ለአንድ ጊዜ ከተሰጣቸው የ15 ኪ.ግ. ፉርኖ ዱቄት ርዳታ ውጭ ያገኙት ነገር እንደሌለ፣ አክለው የተናገሩት አስተባባሪው፣ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል፡፡

የተጠቀሰውን የሟቾች አኀዝ በሪፖርት እንደሚያውቀው ያረጋገጠው፣ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤትም፣ ለክልሉ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ማሳወቁን ገልጿል፡፡ ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ የተፈናቃዮቹ ቅሬታ ትክክለኛ እንደኾነ አምኖ፣ በቅርቡ፣ የዕለት ምግብ ርዳታ ለመላክ ማቀዱን አመልክቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG