በእስራኤል መንግሥት እና በታጣቂው የሐማስ ቡድን መካከል የተደረገውን የተኩስ አቁም ተከትሎ፣ የአራት ዓመቷ እስራኤላዊት አሜሪካዊት ሕፃን፣ ትላንት እሑድ ተለቃለች፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲራዘም ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ፣ የልጅቱን መፈታት አወድሰዋል።
የቪኦኤ ዘጋቢ ቬሮኒካ ባደራስ እግሊሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ ደረጀ ደስታ ወደ ዐማርኛ መልሶታል፡፡