በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወልዲያ ማረሚያ ቤት ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በርካታ ታሳሪዎች እንዳመለጡ ተነገረ


በወልዲያ ማረሚያ ቤት ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በርካታ ታሳሪዎች እንዳመለጡ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:26 0:00

በዐማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን የወልዲያ ከተማ ማረሚያ ቤት ላይ፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ በተሰነዘረ ጥቃት፣ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ታራሚዎች እንዳመለጡ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ነዋሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በማረሚያ ቤቱ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት፣ ከአንድ ሰዓት በላይ የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል፡፡ የፋኖ ታጣቂዎች ጥቃቱን እንደፈፀሙት ነዋሪዎቹ አመላክተዋል። በዚኹ ጥቃት፣ በርካታ ታሳሪዎችን ማስለቀቃቸውንም ገልጸዋል፡፡

በጸጥታ ጉዳይ፣ መረጃ እና ማብራሪያ የሚሰጠው የአካባቢው ኮማንድ ፖስት፣ በጥቃቱ ላይ እስከ አሁን ያለው ነገር የለም፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢዎች በጉዳዩ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎችን አነጋግረዋል። አስማማው አይነው ያቀርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG