በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሥራ ፈጣሪ ማኅበረሰብ” መሥራች ወጣቶቹ በጎ ተጽእኗቸውን በአገሪቱ ለማስፋት ተነሣስተዋል


“ሥራ ፈጣሪ ማኅበረሰብ” መሥራች ወጣቶቹ በጎ ተጽእኗቸውን በአገሪቱ ለማስፋት ተነሣስተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:22 0:00

“ሥራ ፈጣሪ ማኅበረሰብ” መሥራች ወጣቶቹ በጎ ተጽእኗቸውን በአገሪቱ ለማስፋት ተነሣስተዋል

በዐዲስ አበባ ከተማ፣ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች፣ “ዘ ዲስረፕተርስ ዴን” የተሰኘ ማኅበረሰብ መሥርተው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ወጣቶቹ በየሳምንቱ አንዴ፣ “ኤኤልኤክስ ኢትዮጵያ” የተሰኘ ተቋም ባመቻቸላቸው ስፍራ እየተሰባሰቡ ያጋጠሟቸውን ችግሮች፣ ተግዳሮቶች እና በጎ ልምዶች ይጋራሉ፡፡
“ዲስረፕተርስ”፥ በዐውዳዊ ትርጉሙ ሲታይ፣ ያለውንና ነባሩን የሚለውጥ፣ የሚቀይር ማለት ነው፡፡ የሥራ ፈጣሪ ማኅበረሰቡ፣ በንግዱ ዘርፍ ትስስርን በመፍጠር እና በመረዳዳት አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደር የሚችል ማኅበረሰብን የመገንባት ሕልም ይዞ እየሠራ ይገኛል፡፡
በመላው ኢትዮጵያ በጎ ተጽእኖውን ለማስፋፋት አልሞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው “ዘ ዲስረፕተርስ ዴን”፣በአሁኑ ወቅት፣ በአዳማ እና በሐዋሳ ከተሞች ሥራ ለመጀመር ሲዘጋጅ፣ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ካሉ ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች ጋራም ለመቀናጀት በመነጋገር ላይ ነው፡፡
አጋር መሥራቾቹ፣ ዶር. ታምራት ሱልጣንና አቤኔዘር ባዬ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG