በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ“ታላቁ ሩጫ” ላይ የተሳተፉ ከ12 በላይ ወጣቶች እንደታሰሩ ጠበቃቸው ገለጹ


በ“ታላቁ ሩጫ” ላይ የተሳተፉ ከ12 በላይ ወጣቶች እንደታሰሩ ጠበቃቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:23 0:00

ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ በዐዲስ አበባ ከተማ በተካሔደው 23ኛው ዙር “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” ላይ የተሳተፉ ወጣቶች፣ “ሁከት እና ብጥብጥ ማነሣሣት” በሚል ለእስር እንደተዳረጉ፣ ጠበቃቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

ወጣቶቹ በምርመራ ወቅት፣ “የፖለቲካ መልዕክት ያለው ዘፈን ዘፍናችኋል፤” እንደተባሉ፣ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል፡፡

ከታሳሪዎቹ መካከል አራቱ ቲክታከሮች እና ዩቲዩበሮች እንደኾኑ ጠበቃው ጠቅሰው፣ ከእሑድ ጀምሮ በተለያዩ ቀናት የተያዙ ቢኾኑም፣ እስከ አሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ አመልክተዋል፡፡

አንድ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር አባልም፣ ከታላቁ ሩጫ ጋራ በተገናኘ ከውድድሩ በፊት ታስረው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ እንደሚገኙ፣ የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ቀለብ ስዩም ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG