በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የጸጥታ ችግር የወባ ሕሙማንን ቁጥር በዕጥፍ እንደጨመረ ተነገረ


በዐማራ ክልል የጸጥታ ችግር የወባ ሕሙማንን ቁጥር በዕጥፍ እንደጨመረ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:54 0:00

በዐማራ ክልል፣ በወቅታዊው የጸጥታ ችግር ምክንያት፣ ኅብረተሰቡ በየአካባቢው የመከላከል እና የቁጥጥር ሥራ ባለመሥራቱ፣ የወባ በሽታ ታማሚዎች ቁጥር በእጅግ ከፍተኛ አኀዝ እንደጨመረ፣ የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ባለፈው ሳምንት ብቻ፣ የሕሙማኑ ቁጥር በ26 በመቶ እንደጨመረ ያስታወሱት፣ በኢንስቲትዩቱ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋራ ሲነጻጸር በዕጥፍ እንደተስፋፋ ያሳያል፤ ብለዋል፡፡

ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ እስከ አሁን፣ 455ሺሕ የወባ በሽታ ሕሙማን እንደተመዘገቡና ከእነርሱም የ11 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ፣ አስተባባሪው አስታውቀዋል፡፡

ከፍተኛ የመድኃኒት እጥረትም መኖሩን የጠቆሙት አቶ ዳምጤ፣ ያለውም በፍጥነት እንዳይሰራጭ፣ በወቅታዊው የጸጥታ ችግር የመንገዶች መዘጋት ዕንቅፋት እንደፈጠረ አመልክተዋል፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ወረዳ የጤና ጽ/ቤት ሓላፊ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በመተማ ሆስፒታል ያሉ ሐኪሞችም፣ የመድኃኒት እጥረቱ እንዳለ አረጋግጠውልናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG