በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጋዛ ሺፋ ሆስፒታል ያለጊዜያቸው የተወለዱ ህጻናት ለቀው ወጡ


በጋዛ አልሺፋ ሆስፒታል ህዳር 2016
በጋዛ አልሺፋ ሆስፒታል ህዳር 2016

የአለም የጤና ድርጅት በትንሹ 31 በጠና የታመሙ፣ ያለጊዜው የተወለዱ ሕፃናት ከጋዛ ሺፋ ሆስፒታል ወደ ግብፅ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ዛሬ እሁድ አስታውቋል።

የእስራኤል ወታደሮች በሀማስ ታጣቂዎች ላይ ባደረጉት ወታደራዊ ዘመቻ ባለፈው ሳምንት ሆስፒታሉ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት ልዑክ ትላንት ቅዳሜ ሆስፒታሉን ከጎበኘ በኋላ “በአንድ ወቅት በጋዛ ውስጥ ትልቁ ፣ እጅግ የላቀ እና ጥራት ያላቸው የህክምና መሳሪያዎች የነበሩት ሆስፒታል” አሁን “የሞት ቀጠና” ሆኗል ሲል አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር በሺፋ ሆስፒታል ውስጥ የሀማስ ማዘዣ ማእከል ነው ብሎ ያመነውን ማዕከል በህንፃው ስር ይገኛል በሚል በሆስፒታሉ ውስጥ ፍለጋ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ሀማስ እና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ግን ይኸ እውነት አይደለም ሲሉ አጣጥለውታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ጥቃት በአንድ ሌሊት ሁለት ፍልስጤማውያን ሞተዋል።

በሌላ በኩል በሰሜን ጋዛ በሚገኘው ጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ የተካሄደውን የእስራኤል ወታደራዊ እርምጃን ጨምሮ ትላንት ቅዳሜ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ፍልስጤማውያን ሲቪሎች ተገድለዋል፤ እንዲሁም ቆስለዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች የእርዳታ እና ስራዎች ኤጀንሲ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG