በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ድሮኖች በዩክሬን የኃይል አቅርቦቶች ላይ ጥቃት አደረሱ


የዩክሬን ወታደር ህዳር 2016
የዩክሬን ወታደር ህዳር 2016

የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር በሩሲያ የዩክሬን ላይወረራ ላይ በየቀኑ በሚያወጣው የስለላ መረጃ ሩሲያ የሶቪየት ዘመን ከፍተኛ ከፍታ ያለው የስለላ አውሮፕላኖችን ወደ አገልግሎት ለማምጣት እያሰበች ነው ሲል አስታወቀ።

የዩክሬን ባለስልጣናት ትላንትቅዳሜ ከባድ የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የመሠረተ ልማት አውታሮችን ጥቃት አድርሰዋል። በጥቃቱ የተነሳም ከ400 በሚበልጡ ከተሞች እና መንደሮች ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ አስከትሏ በማለት ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የዩክሬን አየር መከላከያ ትላንት ማምሻውን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት እስከ ንጋት 10 ሰዓት ባለው ጊዜ ከ38ቱ ኢራን ሰራሽ ሻሄድ ሰው አልባ አውሮፕላኖች መካከል 29ኙን መተው ጥለዋል።

በተያያዘ የዩክሬን የኃይል አቅርቦት ሚኒስቴር ሩሲያ ባደረሰችው ጥቃት በደቡባዊ ኦዴሳ ክልል 416 ሰፈራዎች እና በደቡብ ምስራቅ ዛፖሪዝሂያ ክልል ውስጥ ኔትወርኮች ከተበላሹ በኋላ ኤሌክትሪክ ተቋርጧል፤ በተጨማሪም በኦዴሳ ክልል የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካም ተመቷል ሲል አስታውቋል።

የዩክሬን ባለሥልጣናት ነዋሪዎች እና የንግድ ድርጅቶች በክረምቱ መጀመሪያ ላይ ሩሲያ በኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማቶች ላይ ልታደርሳቸው ለምትችላቸው አዳዲስ ጥቃቶች እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG