በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሱዳን ሸሽተው ቻድ የገቡ ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ እጦት ገጥሟቸዋል ተባለ


በቻድ ከሚገኙ የፍልሰትኞች መጠለያዎች አንዱ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)
በቻድ ከሚገኙ የፍልሰትኞች መጠለያዎች አንዱ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)

ቤተሰቦቻቸው በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት ሸሽተው ቻድ የገቡ በሺሕ የሚቆጠሩ ሕጻናት፣ ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጦት እንደገጠማቸው ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ አስታወቀ።

ከሱዳን ጎረቤት አገራት ሁሉ ቻድ የበለጠ የሱዳን ፍልሰተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ነች፡፡ በያዝነው የፈረንጆች ወር የመጀመሪያ ሳምንት ብቻ 8ሺሕ ሰዎች ከሱዳን ወደ ቻድ ገብተዋል። ቻድ በአሁኑ ወቅት 900 ሺሕ ሱዳናውያንን በማስተናገድ ላይ ነች፡፡ በዳርፉር ክልል ግጭቱ በማየሉ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የፍልሰተኞቹ ቁጥር ሊጨምር ችሏል።

ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን እንዳስታወቀው፣ ዕድሚያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑት ሕፃናት ውስጥ 13.6 በመቶ የሚሆኑት የተመጣጠነ ምግብ እጦት ይታይባቸዋል።

ቡድኑ 14ሺሕ የሚሆኑትን መርዳቱን፣ 3ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ አስጊ ሁኔታ ውስጥ በመሆናቸው በሆስፒታል እንዲቆዩ መደረጉን አስታውቋል።

በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት 10ሺሕ 400 የሚሆኑ ሰዎች ሲገደሉ፣ 4.8 ሚሊዮን ሰዎች የአገር ውስጥ ተፈናቃይ ሆነዋል። 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት ሸሽተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG