በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብልጽግና ፓርቲ ከተፎካካሪዎች ለመነጋገር ዝግጁ መኾኑን አስታወቀ


ብልጽግና ፓርቲ ከተፎካካሪዎች ለመነጋገር ዝግጁ መኾኑን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:09 0:00

ገዥው ፓርቲ ብልጽግና፣ በአገሪቱ ችግሮች ላይ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ ለመወያየት፣ ዝግጁ መኾኑን አስታወቀ።

የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ሓላፊ ፈዲላ አባቢያ፣ በትላንትናው ዘገባችን፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባቀረቡት ቅሬታ ጉዳይ፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ገዥው ፓርቲ፣ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ በአገሪቱ ባሉት ግጭቶች እና በሚከተሏቸው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጆች የተነሳ፣ “እንቅስቃሴያችን ተገድቧል” ሲሉ፤ የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ሐላፊዋ ደግሞ፣ ለዐዋጆቹ መውጣት መንሥኤ የኾኑትን ችግሮች ለመፍታት በጋራ እንሥራ፤ ብለዋል፡፡

ፓርቲዎቹ፣ “የፖለቲካ ምኅዳሩ ጠቧል፤” ሲሉ ላነሡት ቅሬታም ሐላፊዋ ሲመልሱ፣ “ምኅዳሩ የሚጠበቀውን ያህል ላይሰፋ ይችላል፤ ነገር ግን፣ በዘርፉ ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ነገር አለ፤” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG