በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የጸጥታ ችግር ያባባሰው የምግብ እጥረት ለተማሪዎች ተወዳዳሪነት እንደሚያሰጋ ተገለጸ


በዐማራ ክልል የጸጥታ ችግር ያባባሰው የምግብ እጥረት ለተማሪዎች ተወዳዳሪነት እንደሚያሰጋ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:05 0:00

በዐማራ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች ያጋጠመው የምግብ እጥረት፣ በመማር ማስተማሩ ሒደት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደፈጠረ፣ የዞኖቹ አስተዳደሮች አስታወቁ፡፡ ችግሩ፣ በተለይ በክልሉ ምሥራቃዊ ዞኖች በስፋት እንደሚስተዋል፣ ዞኖቹ ገልጸዋል፡፡

ወቅቱን ባልጠበቀው ዝናም፣ በተባይ፣ በግሪሳ ወፍ እና በተስፋፋው የጸጥታ ችግር የተከሠተው የምግብ እጥረት፣ አሁን እንደተባባሰ ታውቋል፡፡ ይህም፣ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ እያስገደደ እንደኾነና ተማሪዎችም በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳይገኙ ማድረጉ ተገልጿል፡፡ የትምህርት ቤቶቹ ምገባም አነስተኛ እና ተማሪዎችን ለማቆየት እንደማይችል ተመልክቷል፡፡

በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕርግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ፣ ችግሩ መኖሩን አምነው፣ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ያስከተሉት የምግብ እጥረት፣ በቢሮው ዐቅም ብቻ እንደማይፈታ ጠቁመዋል፡፡ ይኹንና፣ የትምህርት ቤቶችን የተማሪዎች ምገባ፣ በበጀት የሚደግፉ ወረዳዎችን ተሞክሮ ለማስፋት ይሠራል፤ ብለዋል፡፡

የትምህርት ባለሞያዎች ደግሞ፣ የክልሉ የጸጥታ ችግር እና የምግብ እጥረት፣ በክልሉ ተማሪዎች ብቁ ተወዳዳሪነት ላይ ተጽእኖ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋታቸውን አጋርተዋል፡፡

ዘገባው የመስፍን አራጌ ነው። አስማማው አየነው በድምፅ አንብቦታል።

XS
SM
MD
LG