በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት “እንቅስቃሴያችንን ገድቦታል” ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር ጥሪ አደረጉ


ግጭት “እንቅስቃሴያችንን ገድቦታል” ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር ጥሪ አደረጉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የትጥቅ ግጭት እና አለመረጋጋት እንቅስቃሴያቸውን እንደገደበባቸው፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ገለጹ፡፡

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አሁን ባለው ግጭት እና አለመረጋጋት ምክንያት፣ በየቦታው ተንቀሳቅሰው አባሎቻቸውንና ደጋፊዎቻቸውን መሰብሰብ እና ማነጋገር እንዳልቻሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ ሓላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ደግሞ፣ አሁን ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት፣ በኦሮሚያ እና በዐማራ ክልሎች፣ መደበኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረግን አይደለንም፤ ብለዋል፡፡

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአመራር አባሉ ዶር. መብራቱ ዓለሙም እንዲሁ፣ በጦርነት ምክንያት በተደጋጋሚ የሚወጡት የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጆች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመንቀሳቀስ መብት እና ነጻነት እንደገደቡ ተናግረዋል፡፡

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ ከችግሩ የመውጫ መንገዱ፥ ሰላማዊ ውይይት እና ፖለቲካዊ ድርድር ማድረግ እንደኾነም አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG