በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈጣሪዎቹ የኬንያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሣር የምግብ ዱቄት አመረቱ


ፈጣሪዎቹ የኬንያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሣር የምግብ ዱቄት አመረቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

በኬንያ ስምጥ ሸለቆ፣ የካባራክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ሣርን ወደ ምግብ ዱቄት በመቀየር ለሰው ልጅ የመብል ፍጆታ የሚውልበትን ዐዲስ ዘዴ ፈጥረዋል።

ይኸው ዐዲስ የዱቄት ዐይነት፣ ለብዙ ቤተሰቦች በጣም ውድ ለኾነውና ከበቆሎ ዱቄት ለሚዘጋጀው ኡጋሊ፣ ዋና ግብአት እንደሚኾን ተነግሯል።

ተማሪዎቹ፣ ከሦስት ዓመታት ምርምር እና ሙከራ በኋላ፣ ኢኮ-ስታርች የተባለው ዐዲስ የሣር ዱቄት አስገኝተዋል፡፡ በቅርቡም፣ ከባለሥልጣናት ይኹንታ በማግኘት፣ ምርታቸውን በገበያ ላይ ለማዋል ተስፋ አድርገዋል፡፡

ዐዲሱ የዱቄት ዐይነት፣ ከኡጋሊ መሥሪያው የበቆሎ የዱቄት በአምስት ጊዜ ባነሰ ዋጋ እንደሚሸጥ ተነግሯል፡፡በምግብ ቀውስ ውስጥ እንደኾነች በሚነገርላት ኬንያ፣ ፈጠራው፥ ፍቱንና ወሳኝ ነው፤ ተብሏል፡፡

በብዙ ንጥረ ምግብ ተዋሕዶ የተሰናዳውን ዱቄት በማቅረብ፣ የኡጋሊን ዋጋ መቋቋም ያቃታቸውን ቤተሰቦች ወደ ራት ገበታው እንመልሳቸዋለን፤ ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG