በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት የመረጃ ነጻነት ዐዋጅን እንዲያጸድቅ የመብቶች ኮሚሽኑ ጠየቀ


መንግሥት የመረጃ ነጻነት ዐዋጅን እንዲያጸድቅ የመብቶች ኮሚሽኑ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:48 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት፥ ለብዙኀን መገናኛዎች፣ መረጃ የማግኘት ነጻነትን ያረጋግጣል፤ የተባለውንና በፍትሕ ሚኒስቴር በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የቆየውን፣ የመረጃ ነጻነት ዐዋጅን እንዲያጸድቅ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ፡፡

በኮሚሽኑ፣ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች የሥራ ክፍል ዲሬክተር አቶ ማንያውቃል መኰንን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የመረጃ ነጻነት ዐዋጅ አስፈላጊነት በጥናት ቢረጋገጥም፣ እስከ አሁን ድረስ ግን ዐዋጁ ሊጸድቅ አልቻለም፤ ብለዋል፡፡ በዚኽም፣ በብዙኀን መገናኛው ዘርፍ ልዩ ልዩ ችግሮች እየተስተዋሉ እንደኾኑ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የብዙኀን መገናኛ ባለሞያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ጥበቡ በለጠ በበኩላቸው፣ እየታየ ያለው የመረጃ ነፃነት ዕጦት፣ ዐዋጅ በማውጣት ብቻ እንደማይፈታና ከብዙኀን መገናኛ ሕግ በላይ፣ የአስተሳሰብ ለውጥ ወሳኝ እንደኾነ ጠቁመዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG