በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ አመራሮች “በፓርቲው መዳከም” እየተወዛገቡ ናቸው


የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ አመራሮች “በፓርቲው መዳከም” እየተወዛገቡ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:25 0:00

በሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ አመራሮች መሀከል እንደተፈጠረ በተገለጸው መከፋፈል፣ ፓርቲው በከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ እንደሚገኝ፣ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር እና የውጭ ግንኙነት ሓላፊ እንደኾኑ የሚናገሩት፣ አቶ ጴጥሮስ ዱብሶ አስታውቀዋል።

በተቃርኖ የቆሙትና ዐሥር የሥራ አስፈጻሚ አባላትን በመያዝ በፓርቲው ጸሐፊ አቶ ገነነ ሐሳና የሚመራው ወገን ደግሞ፣ አቶ ጴጥሮስ፥ ፓርቲውን እንደማይወክሉና ፓርቲውን ለማዳከም ከክልሉ መንግሥት ጋራ በማበራቸው በሥራ አስፈጻሚው እንደታገዱ ይገልጻል።

የክልሉ የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ በበኩሉ፣ በፓርቲው መካከል ያለውን ውዝግብ፣ ከክልሉ መንግሥት ጋራ ለማያያዝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ተከላክሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG