በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን እና ሜድቬዴቭ የሩሲያን ታሪክ በመሣሪያነት አዘጋጁ


የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ፎቶ ፋይል (Jan. 15, 2020.)
የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ፎቶ ፋይል (Jan. 15, 2020.)


የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ በሩሲያ ህዝብ መካከል ፀረ-ምዕራባውያን ስሜቶችን ለማጎልበት እና አጎራባች ምዕራባውያን አገሮችን ለማስፈራራት ታሪክን እንደ ጦር መሣሪያ ለመጠቀም ያዘጋጇቸው ሰነዶች ስጋቶችን አስነስተዋል ሲል የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በወጣው የስለላ መረጃ አመለከተ፡፡

በሚኒስቴሩ በወጣው የስለላ መረጃ ፑቲን “ታሪካዊው የሩሲያውያንና ዩክሬናውያን አንድነት” በሚል ርዕስ ያሰናዷቸው 242 ሰነዶች፣ ከ11ኛ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ያሉትን ታሪኮች የሚያጣቅሱ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ሰነዶቹ ክሬምሊን በዩክሬን ላይ ያላትን ወቅታዊ ፖሊሲ ተገቢነት ለማስረዳት የተደረጉ፣ የፑቲን ጥረቶችና የፕሬዚዳንቱን አስተያየቶች ያካታቱ መሆናቸውን የብሪታኒያው መከላከያ ሚኒስቴር የስለላ መረጃ አመልክቷል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሜድቬድቭ የፖላንድና ሩሲያን ግንኙነት አስመልክቶ ባዘጋጁት ሰነድ፣ “ፖላንድ ሩሲያ ጠል የሆነውን የጠበኝነት ፖሊስ እንደገና ለማስፈን" እየሞከረች ነው ሲሉ የከሰሱበት ጽሁፍ መሆኑንም የሚኒስቴሩ መረጃ ጠቅሷል፡፡

እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ ሩሲያ ፖላንድ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል ያስፈራሩበት ጽሁፍ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ በፓሪስ የሰላም ፎረም ላይ ባሰሙት ንግግራቸው ከሩሲያ ጋር በቀጠለው ግጭት ዓለም አቀፍ ትብብር እና አንድነት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዜለነስኪ በንግግራቸው ጥቂት አገሮች የሁሉንም አገሮች እጣ የሚወስኑበት ብቻ ሳይሆን በዓለም ሀገሮች ሁሉ በእኩልነት ሊታዩ ክብርም ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ለረዥም ጊዜ የሚሆን የ21.4 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተዘግቧል፡፡
ህብረቱ ቀደም ሲል የ26 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም ለዩክሬን ወደ 54 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኢኮኖሚያዊ ርዳታ ለመስጠት ህብረቱ እያሰበ ቢሆንም የአውሮፓ ህዝብ የገንዘብ ድጋፎቹን አስመልክቶ ያደሩበት ስጋቶች እየጨመሩ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG