በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዳባ አራሾች “ከግዳጅ የክረምት ስንዴ ምርት” ባለማትረፋችን ያለማነውን አትክልት “እንዳንሰበስብ ተከለከልን” አሉ

የአዳባ አራሾች “ከግዳጅ የክረምት ስንዴ ምርት” ባለማትረፋችን ያለማነውን አትክልት “እንዳንሰበስብ ተከለከልን” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:36 0:00

የአዳባ አራሾች “ከግዳጅ የክረምት ስንዴ ምርት” ባለማትረፋችን ያለማነውን አትክልት “እንዳንሰበስብ ተከለከልን” አሉ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ፣ በአትክልት ልማት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የዘንድሮውን ምርት ለመሰብሰብ ተቸግረዋል።

አስገዳጅ እንደኾነ ከጠቀሱት የክረምት ስንዴ ተከታታይ አዝመራ ዝቅተኛ ምርት እንዳገኙ የገለጹት አርሶ አደሮቹ፣ ዘንድሮ አትክልት ቢያለሙም ምርቱን እንዳይሰበሰቡ፣ በወረዳው ባለሥልጣናት እንተከለከከሉ አመልክተዋል።

የወረዳው የግብርና ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ዶክተር አብዱላህ ቤካ ደግሞ፣ ለአየር ንብረቱ ተስማሚ የኾኑ ሰብሎች በየተራ እየተመረቱ እንደሚገኙ አስታውቀው፣ አርሶ አደሩ ምርቱን እንዳይሰበሰብ የከለከለው አካል እንደሌለ ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG