በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በታንዛኒያ ሁለተኛ ዙር ድርድር እያካሔዱ መኾኑ ተገለፀ


መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በታንዛኒያ ሁለተኛ ዙር ድርድር እያካሔዱ መኾኑ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:16 0:00

በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሁለተኛ ዙር ድርድር፣ ትላንት ማክሰኞ፣ በታንዛኒያ-ዳሬ ሰላም ከተማ እንደተጀመረ፣ ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በሁለቱም ወገኖች በኩል፣ ዘለቂነት ወዳለው መፍትሔ ለመድረስ የሚታየው ቁርጠኝነት እና ውሳኔ የሚደነቅ መኾኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም ኾነ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ድርድሩ ስለመጀመሩ የሰጡት አስተያየትም ኾነ ያወጡት ይፋዊ መግለጫ የለም።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን፣ ኹለቱ ወገኖች ከስምምነት ለመድረስ እንዲጥሩ አሳስበዋል።

ሁለተኛው ዙር ድርድር እንደተጀመረ እየተነገረ ያለው፣ የመጀመሪያው ዙር ድርድር ያለስምምነት ከተጠናቀቀ ከስድስት ወራት በኋላ ነው። ፀሐይ ዳምጠው ዝርዝር አላት

XS
SM
MD
LG