በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍጋን ገበሬዎች 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አጡ


የአፍጋን ፖሊስ የኦፒየም ተክልን ሲያስወግድ (ፎቶ ፋይል ኤፒ)
የአፍጋን ፖሊስ የኦፒየም ተክልን ሲያስወግድ (ፎቶ ፋይል ኤፒ)

የአፍጋኒስታን ገበሬዎች 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣታቸውን የተመድ የሕገ ወጥ እጾች እና ወንጀል ቢሮ አስታውቋል።

ታሊባን ከአንድ ዓመት በፊት ኦፒየም የተሰኘውን እና ለሄሮይን አደንዛዥ እጽ ምንጭ የሆነውን ተክል ገበሬዎች እንዳያበቅሉ በመከልከሉ ገበሬዎቹ ገቢያቸውን አጥተዋል።

የዓለም ትልቁ የኦፒየም አምራች የሆነችው አፍጋኒስታን፣ ታሊባን ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ለአውሮፓ እና እስያ ዋና የሄሮይን ምንጭ ነበረች።

ታሊባን እገዳውን ከጣለ በኋላ የኦፒየም ምርት 95 በመቶ መቀነሱ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG