በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ዌስት ባንክን ጎበኙ


አንተኒ ብሊንከን ከፍልስጤማውያኑ ፕሬዝደንት ሞሃሙ ሃባስ ጋር (ፎቶ፣ ከፍልስጤም ባለሥልጣን በኤኤፍፒ በኩል የተገኘ ኅዳር 5፣ 2023)
አንተኒ ብሊንከን ከፍልስጤማውያኑ ፕሬዝደንት ሞሃሙ ሃባስ ጋር (ፎቶ፣ ከፍልስጤም ባለሥልጣን በኤኤፍፒ በኩል የተገኘ ኅዳር 5፣ 2023)

የአሜሪካው የወጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ እሁድ በእስራኤል በተያዘችው ዌስት ባንክ ያልተጠበቀ ጉብኝት በማድረግ ከፍልስጤማውያኑ ፕሬዝደንት ሞሃሙ ሃባስ ጋር ተገናኝተዋል።

የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ከጀመረ ወዲህ ለሁለተኛ ግዜ በመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት ያደረጉት ብሊንከን፤ ትናንት ካጣር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅ፣ ጆርዳን እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር አማን ላይ ተነጋግረዋል። በስብሰባው እስራኤል የተኩስ አቁም ላይ እንድትስማማ አሜሪካ ግፊት እንድታደርግ ተጠይቋል።

ብሊንከን በበኩላቸው፣ ተኩስ ማቆም ሐማስን ብቻ የሚጠቅም ጉዳይ እንደሆነና፣ የሚፈይደውም ቢኖር ሐማስ እንደገና ተዘጋጅቶ ጥቃት እንዲሰነዝር ግዜ መስጠት ነው ብለዋል።

ሰዎች ተጨናንቀው በሚኖሩበት በጋዛ ሰርጥ ከተወሰኑ ሥፍራዎች ለቀው መውጣት እንዲችሉ፣ ሰብዓዊ ተኩስ ማቆም እንዲኖር ዋሽንግተን ሃሳብ አቅርባለች። ነግር ግን ይህንንም ሃሳብ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ እንደማይቀበሉ ዓርብ ዕለት ለብሊንከን ገልጸውላቸዋል።

ብሊንከን በግጭቱ ላይ ለመነጋገር ነገ ሰኞ ቱርክ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG