በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በደረሰ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ፣ 20 ሰዎች መሞታቸውን እና 12ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ቤታቸውን ጥለው ለመውጣት መገደዳቸውን የክልሉ መንግስት ትናንት አስታውቋል።
የጣለው ድንገተኛ ዝናብ መንገዶችን እና ድልድዮችን በማፍረሱ፣ ለተጎጂዎች ርዳታ ማድረስ አለመቻሉም ታውቋል።
በእንስሳት፣ ሰብል እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንም የኤኤፍፒ ዜና ወኪል የክልሉን የተግባቦት ቢሮ ጠቅሶ ዘግቧል።
ዝናቡ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመምጣቱ፣ እንዲሁም የአየር ንብረት ትንበያዎች እንደሚያመለክቱት፣ የጎርፍ አደጋ የመከሰቱ ዕድል ከፍተኛ ነው።
ኤል ኒኞ በተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በምሥራቅ አፍሪካ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ድረስ ከተለመደው ከፍ ያለ የዝናብ መጠን እንደሚኖር የተመድ የሰብዓዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ባለፈው ወር አስታውቆ ነበር።
መድረክ / ፎረም