በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ሆስፒታል አቅራቢያ እስራኤል በአምቡላስ ላይ ባደረሰችው ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ


በአምቡላስ ላይ የተፈጸመ ጥቃት ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም በጋዛ
በአምቡላስ ላይ የተፈጸመ ጥቃት ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም በጋዛ

ከተከበበው ሰሜናዊ ጋዛ ቁስለኞችን ለማስወጣት በሚውል አምቡላንስ ላይ እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት ትላንት አርብ 15 ሰዎች ሲሞቱ 60 ሰዎች መቁሰላቸውን በሀማስ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የአካባቢው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የእስራኤል ጦር “የሀማስ አሸባሪ ቡድን እየተጠቀመበት ነው ያለውን” አምቡላንስ በመለየት ማጥቃቱን አስታውቋል። በጥቃቱም የሀማስ ተዋጊዎች ተገድለዋል ያለ ሲሆን፤ ቡድኑ ታጣቂዎችን እና የጦር መሳሪያዎችን በአምቡላንሱ አስተላልፏል ሲል ከሷል።

የሀማስ ባለስልጣን ኢዚት አል ረሺቅ በስፍራው ተዋጊዎቻቸው ነበሩ የሚለውን ክስ ‘መሰረት የለሽ’ በማለት ውድቅ አድርገውታል። በተመሳሳይ የጋዛ የጤና ሚኒስትር አሽራፍ አል ቂድራ አምቡላሱ እስራኤል በጋዛ በሚገኘው አል ሲፋ ሆስፒታል አቅራቢያ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረ ልዑክ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

የእስራኤል ጦር ድርጊቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ አምቡላንሱ ከሀማስ ጋር ግንኙነት አለው ለማለቱ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃ ባይሰጥም ተጨማሪ መረጃዎችን ለመልቀቅ ማቀዱን ግን አስታውቋል።

ዜናውን የዘገበው ሮይተርስ የዜና አውታር የሁለቱንም ወገኖች ሀሳብ በራሱ ማረጋገጥ አለመቻሉን ገልጿል።

በተያያዘ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ "በአምቡላንስ ህሙማንን ከስፍራው እያስወጡ ሳለ በደረሰው የአደጋ ዜና በጣም ተደናግጫለሁ" ያሉ ሲሆን ህሙማን፣ የጤና ባለሙያዎች እና የህክምና ተቋማት ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል በማለት አሳስበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG