የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን በኪየቭ ይገኛሉ። ፕሬዘዳንቷ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 24 /2016 ዓም ያደርጉት ጉብኝት፤ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ዩክሬን ከህብረቱ ጋር አባል ሀገራት ጋር ለመቀላቀል የተገብረቻቸውን አስፈላጊ እርምጃዎች ከማወጁ ከቀናት በፊት ነው።
ዩክሬን በጎርጎሮሳዊያኑ የካቲት 2022 በሩሲያ ከተወረረች ከቀናት በኋላ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ማመልከቷ የሚታወስ ነው።
የአባልነት ሂደቱ ብዙ ጊዜ ዓመታትን የሚወስድ ቢሆንም፤ ነገር ግን ዩክሬን የሩስያን ወረራ በመዋጋት ለአባልነት ወሳኝ እንደሆነ የምትቆጠር ሲሆን በተቻለ ፍጥነት ህብረቱን መቀላቀል ትሻለች።
የአውሮፓ ህብረት ዩክሬን ከቡድኑ ጋር በመጭው ታህሳስ ወር የሚጀመረውን የመቀላቀል ድርድር መጀመር መቻል አለመቻሏን የፊታችን ረቡዕ ይፋ ያደርጋል።
መድረክ / ፎረም