የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት እየቀጠለ ባለበት በዚኽ ወቅት፣ አንዳንድ የአገሪቱ ዜጎች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ከሓላፊነታቸው የመልቀቂያ ጊዜያቸው አሁን እንደኾነ እየተናገሩ ናቸው።
ከአራት ሳምንታት በፊት፣ በሐማስ ለደረሰው ድንገተኛ ጥቃት እና የ1ሺሕ400 እስራኤላውያን ሞት፣ ኔታንያሁ ሓላፊነት ለመውሰድ አይፈልጉም። ከሥልጣናቸውም እንደማይወርዱ በግልጽ ተናግረዋል።
ሊንዳ ግራድስታቲን ከኢየሩሳሌም የላከችው ዘገባ፣ ነው፡፡