በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እና በግጭቱ ክልሎች ያሉ ወጣቶች አስተያየት 


የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እና በግጭቱ ክልሎች ያሉ ወጣቶች አስተያየት 
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:26 0:00

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እና በግጭቱ ክልሎች ያሉ ወጣቶች አስተያየት 

በህወሓት ኃይሎች እና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል በደቡብ አፍሪካ-ፕሪቶርያ የተደረገው ግጭቱን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመቱን ይዟል።

ስምምነቱ እጅግ ብዙ ክፍተቶች እንዳሉበት ቢገለጽም፣ ጦርነቱ ሲካሔድ በቆየባቸው አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ አስችሏል።

በጦርነቱ ተሳታፊ በነበሩት በትግራይ፣ በዐማራ እና በአፋር ክልሎች ያሉ ወጣቶች፣ በሰላም ስምምነቱ አስፈላጊነት ላይ ይስማማሉ። ይኹን እንጂ፣ በፕሪቶርያው ስምምነት ላይ የተለያዩ አቋሞች እንዳሏቸው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡

በተያያዘ፣ ያለፈው አንድ ዓመት፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ኹኔታ፣ በወጣቶች ሥነ ልቡና ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳስከተለ ጥናቶች ማመላከታቸውን፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ክፍል ባልደረባ ዶር. አወቀ ምሕረቱ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡

ከሽግግር ፍትሕ ጋራ በተያያዘም አስተያየታቸውንየሰጡት ዶር. አወቀ፣ በፍርድ ቤት ሒደት ላይ ብቻ ያተኮረ ፍትሕ፣ የበዳይንም ኾነ የተበዳይን የሥነ ልቡና ቁስል እንደማያሽር ገልጸው፣ ማኅበረሰብ ተኮር የእርቅ እና የውይይት መድረኮችን አስፈላጊነት አመልክተዋል።

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG