በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዳቦ እና ብስኩት ዝግጅት መዋል የቻለው "ልዕለ ምግቡ" እንሰት


ለዳቦ እና ብስኩት ዝግጅት መዋል የቻለው "ልዕለ ምግቡ" እንሰት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:03 0:00

ለዳቦ እና ብስኩት ዝግጅት መዋል የቻለው "ልዕለ ምግቡ" እንሰት

በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የሚበቅለው እንሰት፣ በኢትዮጵያ በተለይም በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ለምግብነት ይውላል።
እንሰት ድርቅን በመቋቋምና ረዥም ጊዜ በመቀመጥ፣ እንዲሁም አስከፊ የአየር ንብረት ቀውስን በመቋቋም፣ "ልዕለ ምግብ" እየተሰኘ እስከ መጠራት ደርሷል።
በእንሰት ላይ የመመረቂያ ጽሑፋቸውን የሠሩ ሦስት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም. "ብራይት ማኑፋክቸሪንግ" የተሰኘ ተቋም በመመሥረት የእንሰት ዱቄትን አብላልተው፣ ለልዩ ልዩ ብስኩቶች እና የምግብ ግብዓቶች የሚውል ዱቄት በማምረት፣ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያዎች ለማቅረብ ችለዋል።
ወጣቶቹ፣ ኢትዮጵያ ወደ ሀገር ውስጥ ከምታስገባው የዱቄት ገበያ፣ በትንሹ 20 በመቶውን የመጋራት ሕልም እንዳላቸውም፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። ኤደን ገረመው፣ ከመሥራቾቹ መካከል የኾነውን እሱባለው አለልኝን፣ ስለ ተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴ አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ ይቀጥላል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG