በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዐማራ ክልል ላይ ያወጣውን ሪፖርት አጣጣለ


መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዐማራ ክልል ላይ ያወጣውን ሪፖርት አጣጣለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:47 0:00

· የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎችን በመብቶች ጥሰቶች ወቀሱ

በዐማራ ክልል በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች፣ ግድያን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመ እንደኾነ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ያወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃወመ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶክተር)፣ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የኮሚሽኑን ሪፖርት፣ “ሚዛናዊነት የጎደለውና በመረጃ ላይ ያልተመሠረተ” ሲሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡

ሚኒስትሩ፣ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ሥር በሚገኘው በዐማራ ክልል፣ ከሦስት ሺሕ በላይ ሰዎች እንደታሰሩ ገልጸው፣ ከእኒኽም ውስጥ የሚበዙት በሒደት እየተለቀቁ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ “ሕዝቡ ለጸጥታ ኀይሎች የሚሰጠው ድጋፍ ጨምሯል፤ ስለ መከላከያ ሠራዊት ያለው የተዛባ አመለካከትም ተስተካክሏል፤” ያሉት ዶር. ለገሰ፣ በሁሉም የአስተዳደር ዕርከኖች፣ የሕዝቡን ጥያቄ በድርድር እና በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ የሚችሉ ዐዲስ አመራሮችም እንደተተኩ አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም፣ መርዓዊ እና መሸንቲ ከተሞች፣ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች በሚያደርጉት የቤት ለቤት ፍተሻ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየደረሰባቸው እንደኾነ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የከተሞቹ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች፥ ያልታጠቁ ሰላማዊ ወጣቶችን ይገድላሉ፤ ይደበድባሉ፤ አፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ ይወስዳሉ፤ የግል ንብረትን ሳይቀር ይቀማሉ፤ ሲሉ ከሰዋል፡፡

በዚኽ የተነሳም፣ በየአካባቢያቸው ውጥረቱ እንደተባባሰ ያስረዱት ነዋሪዎቹ፣ ከከተማ መኖሪያቸውን እየወጡ ወደ ጫካ እየተሰደዱ እንደኾነ አክለው ገልጸዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG