በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ አሜሪካዊ ማባያ የቀመመው ተቋም


ኢትዮ አሜሪካዊ ማባያ የቀመመው ተቋም
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:31 0:00

ኢትዮ አሜሪካዊ ማባያ የቀመመው ተቋም

“ኢትዮጵያን ጎርሜ ፉድ”፣ የሚያቃጥለውን የአሜሪካውያን የበርበሬ ሶስ በኢትዮጵያዊ ጣዕም ለማጣፈጥ የቻለ ተቋም ነው።

በሳራ አየለ፣ በአሜሪካዊ ባለቤቷ እና በታናሽ እህቷ አማካይነት፣ ከሦስት ዓመታት በፊት የተጀመረው ድርጅቱ፣ ዐይነተኛ ኢትዮጵያዊ ጣዕም ያለውን የሚያቃጥል ጣዕም ያለውን ሶስ፥ “ኢትዮጵያን ሆት ሶስ” በሚል መለዮ ለገበያ አቅርቧል።

ከመሥራቾቹ አንዷ የኾነችው ሳራ አየለ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራት ቆይታ፣ ኢትዮጵያውያን ያሏቸውን ያልተነኩ ሀብቶች እና ጣዕሞች፣ ከሌሎች ሀገራት ባህላዊ ምግቦች ጋራ ማዋሐድን እንዲለምዱ ትመክራለች። ይኸውም፣ ባህልን ለማስፋት እና የንግድ ትስስርን ለመፍጠር እንደሚረዳ ታመለክታለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘ ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG