ከኢትዮጵያ ባህላዊ አልባሳት ጋራ ተመሳስለው የሚሠሩ የቻይና አልባሳት፣ ከገበያ እያስወጧቸው እንደኾነ የገለጹ ዲዛይነሮች እና ነጋዴዎች፣ ኢፍትሐዊ ባሉት ውድድር ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሚገኝ ተናገሩ፡፡
የቻይና አልባሳት፣ በእጅ ከሚመረቱት የሀገር ውስጥ ባህላዊ አልባሳት ጋራ በውበት እና በጥራት እንደማይመጣጠኑ ያስረዱት ነጋዴዎቹ እና ሸማቾቹ፣ በቅናሽ ዋጋ ግን ስለሚሸጡ ብዙ ሸማች እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
በመኾኑም፣ ፊታቸውን ወደ ቻይና አልባሳት ለማዞር እየተገደዱ እንደኾነም ተናግረዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡