በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት ሳቢያ በቂ ግብር ባልተሰበሰበበት የዐማራ ክልል ተጨማሪ ቀውስ አስግቷል


በግጭት ሳቢያ በቂ ግብር ባልተሰበሰበበት የዐማራ ክልል ተጨማሪ ቀውስ አስግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:16 0:00

በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ ግብር በአግባቡ እንዳልተሰበሰበ የገለጸው የገቢዎች ቢሮ፣ በክልሉ ላይ ችግር እያስከተለ እንደኾነ አመለከተ።

የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ ፍቅረ ማሪያም ደጀኔ፣ ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ሊሰበሰብ ከታሰበው ግብር እስከ አሁን የተከናወነው አንድ ሦስተኛው ብቻ እንደኾነ ተናግረዋል።

ሓላፊው በተለይ፣ ወቅታዊው የሰላም መደፍረስ ተጠናክሮ እንደሚታይባቸው በገለጿቸው የክልሉ ምዕራባዊ አካባቢዎች፣ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ፣ በተጨባጭ ለመሰብሰብ የቻለው ግን፣ 6ነጥብ2 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው፤ ብለዋል፡፡

ይህም ዝቅተኛ ገቢ እንደኾነ የቢሮ ሓላፊው ጠቅሰው፣ ግጭቱ በዚኹ ከቀጠለ፣ ክልሉ፣ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ የመክፈል ዐቅም ሊያጣ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋራ በተያያዘ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎችም፣ በግጭቱ ምክንያት ሱቆቻችን እንደተዘጉ መኾናቸውን አመልክተው፣ “ምን ተሠርቶ ይከፈላል?” ሲሉ በጥያቄ ይመልሳሉ፡፡ የምጣኔ ሀብት ባለሞያው አቶ ይርጋ ተስፋዬ ደግሞ፣ የመንግሥት ግብር አለመሰብሰብ፣ በክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ጠቁመዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG