በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ “የሰብአዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ ናት” ሲሉ የመብቶች ተሟጋቾች ገለጹ


ኢትዮጵያ “የሰብአዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ ናት” ሲሉ የመብቶች ተሟጋቾች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:33 0:00

በኢትዮጵያ በርካታ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈጸመ የገለጹ ልዩ ልዩ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት፣ አገሪቱ በሰብአዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ አስታወቁ፡፡

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን፣ ትላንት እሑድ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባልደረባ ዶር. ብራይትማን ገብረ ሚካኤል፣ በጦርነት እና በግጭት፣ በድርቅ፣ በቤቶች ፈረሳ እና በሌሎችም ምክንያቶች፣ በአገሪቱ የተለያዩ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈጸመ አትተው፣ በአጠቃላይ አገሪቱ፣ በሰብአዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ምክትል ዋና ዲሬክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች፣ የዜጎች ፖለቲካዊ እና የሲቪል መብቶች እየተጣሱ እንዳሉ ጠቅሰው፣ መንግሥት የዜጎችን መብቶች የማክበር እና የማስከበር ሐላፊነቱን እየተወጣ እንዳልኾነ አመልክተዋል፡፡

የቀድሞው የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሕግ ምሁሩ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊም፣ በኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቆጣጠሩ ተቋማት ያለመኖር፣ ችግሩን እንዳባባሰው አስገንዝበው፣ “እንደ ሀገር ፈተና ላይ ወድቀናል፤” ብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG