በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

18 ሰዎችን ተኩሶ የገደለው ካርድ ራሱን ገድሎ ተገኘ


ሮበርት ካርድ
ሮበርት ካርድ

ዩናይትድ ስቴትስ ሜይን ክፍለ ግዛት ውስጥ ባለፈው ረቡዕ በከፈተው የጅምላ ተኩስ 18 ሰዎችን ገድሎ 13ቱን በማቁሰል ሲታደን የቆየው ሮበርት ካርድ ትናንት ምሽት ሞቶ ተገኝቷል፡፡

ባለሥልጣናት ራሱን በጥይት መትቶ ገድሏል ያሉት የካርድ አስክሬን የተገኘው ትናንት ዓርብ፣ ከምሽቱ ለሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ላይ፣ በሜይን ግዛት፣ ሊዝቦን ፎልሰቸርች ውስጥ በሚገኘው አንድሮስኮጊን ወንዝ ዳርቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአእምሮ ጤንነት እክል እንደነበረው የተነገረለት የ40 ዓመቱ ካርድ ቀድሞ የሠራዊት አባልና ኋላም የጦር መሣሪያ ተኩስ አሠልጣኝ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ህግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ራሱን ከመግደሉ በፊት ለወንድ ልጁ ትቶ የሄደ ማስታወሻ መኖሩን ቢገልጹም ዝርዝሩም ሆነ ግድያውን የፈጸመበት ግልጽ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም ሲል የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG