በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ዋሻዎችና ምሽጎችን በመደብደብ በጦርነቱ እየገፋች መሆኗን አስታወቀች


ፍልስጤማውያን እስራኤል እኤአ ጥቅምት 27 በጋዛ ያደረሰችውን የአየር ጥቃት ሲመለከቱ
ፍልስጤማውያን እስራኤል እኤአ ጥቅምት 27 በጋዛ ያደረሰችውን የአየር ጥቃት ሲመለከቱ

እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን የአየር እና የምድር ጥቃቷን በማስፋፋት፣ በርካታ የመሬት ውስጥ መተላለፊያ ዋሻዎች፣ ምሽጎችንና የመገናኛ አውታሮችን ማውደሟን አስታወቀች፡፡

እስራኤል በምታካሂደው ስትራቴጂክ ጦርነት እየተራመደች ነው ያሉትየሠራዊቱ ቃል አቀባይወታደሮችዋ በተሰማሩበት ይቆያሉብለዋል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ባለሥልጣናት ቴል አቪቭ ምግብ፣ ውሃ እና መድሀኒት የጫኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች ዛሬ ቅዳሜ ወደ ጋዛ እንዲገቡ ትፈቅዳለች ብለዋል፡፡

ይህ መባሉ ቢያንስ አንስተኛ እርዳታ ይገባበታል በሚባለውና ከግብፅ ጋር በሚዋሰነው አካባቢ የቦምብ ድብደባው ጋብ ሊል እንደሚችል ፍንጭ መስጠቱ ተነግሯል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ዓርብ በእስራኤል እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል አፋጣኝ የሰብአዊነት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቋል።

ዩናይትድ ስቴትስም ለሲቪሎች ሰብአዊ ርዳታ፣ ነዳጅ እና ኤሌክትሪክ ተደራሽነት እንዲመቻች በጋዛ የእስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቆም ድጋ ስትገልጽ በግጭቱ ወቅት ማስ የታፈኑ 200 በላይ ታጋቾች እንዲለቀቁም ጠይቃለች፡፡

እስራኤል ሌሊቱን ባካሄደችው የአየር ድብደባ፣ በአየር ለሚሰነዘሩ ማስ ጥቃቶች ይውላሉ የተባሉትን መሳሪያዎች መደብደቧን ገልጻለች፡፡

በድብደባው የአየር ጥቃቱን ይመራሉ የተባሉት ማስ ቡድን መሪ፣ አሴም አቡ ራካባ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ የእስራኤል መከላከያ ባለሥልጣናት በቀድሞ ትዊተር ባሁኑ X ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡

እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን የአየር እና የምድር ጥቃት እያሰፋች ባለችበት ወቅት እግረኛ ወታደሮችዋን ወደ ጋዛ ለማስገባት እየተዘጋጀች ያለችውን የእስራኤል ጦር፣ ማስበሙሉ ኃይሉለመጋፈጥ ቃል ገብቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG