በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐዲያ ደሞዝ ያልተከፈላቸው የሆስፒታል ሠራተኞች ሥራ በማቆማቸው ነዋሪዎች መቸገራቸውን ገለፁ


 በሐዲያ ደሞዝ ያልተከፈላቸው የሆስፒታል ሠራተኞች ሥራ በማቆማቸው ነዋሪዎች መቸገራቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:07 0:00

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን የሾኔ ከተማ ነዋሪዎች፣ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ በማቆሙ፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጠ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።

በተመሳሳይ የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ ትምህርት አለመጀመሩን የተናገሩ አስተያየት ሰጪዎች፣ “ልጆቻችን በትምህርት ወደ ኋላ እየቀሩብን ነው፤” ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እና ምላሽ እንዲሰጡን፣ ከወረዳው እስከ ክልል ባለሥልጣናት ድረስ ስልክ ያደረግነው የስልክ ሙከራ አልተሳካም። ይኹን እንጂ፣ የሐዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ፣ ችግሩ በበጀት እጥረት እንደተፈጠረና ለመፍታትም ጥረት እየተደረገ እንደኾነ፣ ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር።

ችግሩ በተደጋጋሚ እንደሚከሠት የጠቀሰው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ በበኩሉ፣ አግባብነት እንደሌለውና መንግሥት አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥበት አሳስቧል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበርም፣ ችግሩን እንደሚያውቀው ገልጾ፣ ከመንግሥት ጋራ በመነጋገር እንደሚፈታው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG