በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች ተገቢ እንዳልኾኑ ሚኒስትሩ ተቃወሙ


በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች ተገቢ እንዳልኾኑ ሚኒስትሩ ተቃወሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00

በኢትዮጵያ፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ገና በዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንዳለ የገለጹት የፍትሕ ሚኒስትሩ፣ በሒደቱ ላይ ትችቶች የመቅረባቸውን ተገቢነት ተቃወሙ፡፡

በአንጻሩ፣ በሽግግር ፍትሕ ሒደት ላይ የገለልተኝነት ጥያቄ እንዳላቸው፣ ልዩ ልዩ አካላት እየገለጹ ሲኾን፣ ከእኒኽም መካከል የትግራይ ክልል ይጠቀሳል፡፡

አሁን ያሉት የአገሪቱ ተቋማት፣ የሽግግር ፍትሕ ሒደቱን ለማስፈጸም የገለልተኝነት ችግር እንዳለባቸው፣ ሰሞኑን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ ምልልስ የገለጹት፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ዐማኑኤል አሰፋ፣ በፖሊሲ ዝግጅቱም ላይ ክልሉ እየተሳተፈ እንዳልኾነ ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ከገለልተኝነት ጋራ የተያያዙ የአካሔድ ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙት፣ በፖሊሲው ነው፤ ያሉት የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶር. ጌዴዎን ጢሞቲዎስ፣ በፖሊሲው ዝግጅት ሒደት ላይ፣ የትግራይ ክልልን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች እንደተሳተፉ አውስተዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ፣ በዝግጅቱ እና በሒደቱ ላይ ሐሳብ አለኝ የሚል አካል፣ ሐሳቡን ማቅረብ እንደሚችል ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG