በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጋዛን፣ ሶሪያን እና የሌባኖስን ድንበር ደበደበች


እስራኤል በጋዛ ላይ የፈጸመችውን ድብደባ የሚያሳይ (ፎቶ ኤኤፍፒ ጥቅምት 22፣ 2023)
እስራኤል በጋዛ ላይ የፈጸመችውን ድብደባ የሚያሳይ (ፎቶ ኤኤፍፒ ጥቅምት 22፣ 2023)

እስራኤል ትናንት ሌሊት የጋዛ ሰርጥን፣ በሶሪያ የሚገኙ ሁለት የአየር ማረፊያዎችን፣ እንዲሁም የሌባኖስ ድንበር አካባቢን ደብድባለች፡፡ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የሚካሄደው ግጭት ወደ ሰፊ የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚለው ስጋት እያየለ መጥቷል።

በአሌፖ እና ደማስቆ የአየር ማረፊያዎች ላይ የሚደረገው ድብደባ፣ ከኢራን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ መሣሪያ እንዳይገባ ለማገድ ነው ስትል እስራኤል አስታውቃለች፡፡

በጋዛ በተፈጸመው ድብደባ፣ ማምሻውን ብቻ 55 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል።

አንድ በዌስት ባንክ የሚገኝ መስጊድን መምታቱን እና፣ መስጊዱ ሐማስ እና የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ ጥቃት ለማድረስ ሲያቅዱበት የነበረ ስፍራ ነው ሲል የእስራእል ጦር አስታውቋል።

በሌባኖስ ድንበር አካባቢ ያሉ እስራኤላውያን እንዲወጡ እንደሚደረግ እስራኤል አስታውቃለች። አካባቢው የሀማስ እና የሄዝቦላ የሚሳኤል ጥቃት ኢላማ ሆኗል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ትናንት በካይሮ ሲደረግ የነበረውና በግጭቱ ላይ ሲመክር የነበረው ጉባኤ ካለ ስምምነት ተጠናቋል።

እስራኤላውያን ወደ ግብጽ፣ ዮርዳኖስ እና ሞሮኮ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ እና በእነዚህ ሀገራት የሚገኙም ከሆነ በአስቸኳይ እንዲወጡ የእስራኤል መንግስት ጥሪ አድርጓል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG