በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
የእስራኤል-ሐማስ ግጭትን በተመለከተ በዓለም ዙሪያ የሚደረገው የድጋፍ እና ተቃውሞ ሰልፍ ቀጥሏል

የእስራኤል-ሐማስ ግጭትን በተመለከተ በዓለም ዙሪያ የሚደረገው የድጋፍ እና ተቃውሞ ሰልፍ ቀጥሏል


በጀርመን እስራኤልን በመደገፍ የተደረገ ሰልፍ (ፎቶ ኤፒ ጥቅምት 22፣ 2023)
በጀርመን እስራኤልን በመደገፍ የተደረገ ሰልፍ (ፎቶ ኤፒ ጥቅምት 22፣ 2023)

በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች እስራኤልን ለመደገፍ እና በአይሁዶች ላይ የሚታይ ያሉትን ጥላቻ በመቃወም በበርሊን እና በለንደን ሰልፍ አድርገውዋል።

በሌላ በኩል በከበባ ውስጥ ባለችው ጋዛ ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን በዓለም ዙሪያ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ እንደቀጠለ ነው።

በለንደን ከተማ 100 ሺሕ የሚገመቱ ሰልፈኞች እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ድብደባ እንድታቆም በመጠየቅ ሰልፍ ወጥተዋል።

በበርሊን እስራኤልን ለመደገፍ የወጡት ሰልፈኞች፣ የእስራኤልን ባንዲራ እና በሐማስ የታገቱት ሰዎች ፎቶግራፍ ይዘው ታይተዋል።

የጀርመኑ ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ለሰልፈኞቹ ባደረጉት ንግግር፣ “አይሁዳውያን አሁንም ጀርመን ውስጥ በስጋት ውስጥ መኖራቸው ተቀባይነት የለውም። በጀርመን በእያንዳንዱ አይሁድ እና የአይሁድ ተቋም ላይ የሚሰነዘር ጥቃት ለሃገሪቱ ውርደት ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

በለንደን የእንግሊዝ አይሁዶች ቦርድ ሊቀመንበር፣ ሰልፈኞች በሐማስ የታገቱት 200 ሰዎች እንዲለቀቁ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በበርሊን አይሁዳውያን የሚኖሩባቸው በርካታ ሕንጻዎች “የዳዊት ኮከብ” ተብሎ የሚጠራው የእስራኤል ባንዲራ አርማ ምልክት የተደረገባቸው ሲሆን፣ ባለፈው ሣምንት በአንድ የእስራኤል የእምነት ተቋም ወይም ሲናጋግ ላይ ሁለት የሞሎቶቭ ኮክቴል ተወርውሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG