በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒዤር፤ ሁንታው ባዙም ሊያመልጡ ነበር ቢልም፣ በመኖሪያቸው በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ ዘመዳቸው አስታወቁ


ሞሃመድ ባዙም (ፎቶ ፋይል ኤኤፍፒ)
ሞሃመድ ባዙም (ፎቶ ፋይል ኤኤፍፒ)

በኒዤር በመፈንቅለ መንግስት የተወገዱት ፕሬዝደንት ሞሃሙድ ባዙም ሊያመልጡ ሞክረዋል ሲል ወታደራዊው ሁንታ በቅርቡ ቢያስታውቅም፣ አንድ ዘመዳቸው ግን ከቤተሰባቸው ጋር በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

በኒያሜይ ፕሬዝደንታዊ መኖሪያ ከባለቤታቸውን እና ከልጃቸው ጋር እንደሚገኙ የቅርብ ቤተሰቡ ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል። ስልክ ለመደወልም እንደተፈቀደላቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ባዙም ሊያመልጡ ሞክረው እንደከሸፈባቸው ወታደራዊ ሁንታው ባለፈው ሐሙስ አስታውቆ ነበር።

“ወደ ኒያሜይ ዳርቻ ሸሽተው፣ ከዛም በሌላ ሀገር ርዳታ በሄሊኮፕተር ወደ ናይጄሪያ ሊሸሹ ነበር” ሲል ሁንታው አስታውቆ፣ ድርጊቱን ሊፈጽሙ የነበሩት ዋና ተዋናዮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል።

ባዙምን የሚወክሉት ጠበቆች፣ የሁንታው መግለጫ የፈጠራ ወሬ ነው በማለት፣ ባዙም ከሰው ጋር እንዳይገናኙ ተደርገው ተይዘዋል ብለዋል።

ጠበቆቹ ባዙም ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ሲሉ ሕጋዊ ጥያቂያቸውን ለቀጠናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ባለፈው ወር አስገብተዋል።

ባዙምን ወደ ስልጣናቸው ለመመለስ የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የማይሳካ ከሆነ፣ በወታደራዊ መንገድ ጣልቃ እንደሚገባ ኤኮዋስ አስጠንቅቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG