አንድ የቻይና እና ሌላ የፊሊፒንስ መርከቦች በደቡብ ቻይና ባሕር ላይ መጋጨታቸውን ተከትሎ፣ ሁለቱ ሀገራት አንደኛው ሌላውን ለግጭቱ ተጠያቂ አድርጓል።
ክስተቱ የአካባቢው ሀገራት በይገባኛል በሚጨቃጨቁበት በደቡብ ቻይና ባሕር ከሚደረገው ፍጥጫ እና መጎሻሸም አዲሱ እንደሆነ ተዘግቧል።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያገለገለው አሮጌው የፊሊፒንሱ መርከብ፣ በአካባቢው ለተሠማራው የሀገሪቱ ጦር ስንቅና ትጥቅ በማቀበል ላይ ነበር ተብሏል። ዛሬ ማለዳ መጠነኛ ግጭት ተከስቶ ነበር ያለው የቻይና የባሕር ድንበር ጥበቃ፣ መርከቡን ያገደው “ሕገወጥ የግንባታ መሣሪያ” በሥፍራው ለሚገኘው የጦር መርከብ ሲያስተላልፍ ስለነበር ነው ብሏል።
የፊሊፒንስን ህጋዊ የባሕር ላይ እንቅስቃሴ ቻይና በማወክ ላይ ነች ስትል አሜሪካ ለፊሊፒንስ ያላትን ድጋፉን ገልጻለች።
መድረክ / ፎረም