በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ዛሬም ጋዛን ከአየር ስትደበድብ አድራለች


በሰሜን ጋዛ ሰርጥ የደርሰ የእስራኤልድብደባ (ፎቶ ኤኤፍፒ ጥቅምት 20፣ 2023)
በሰሜን ጋዛ ሰርጥ የደርሰ የእስራኤልድብደባ (ፎቶ ኤኤፍፒ ጥቅምት 20፣ 2023)

እስራኤል በመላ ጋዛ ባሉ ኢላማዎች ላይ የምታደርገውን ድብደባ ዛሬም ቀጥላለች።

“የሰላም ምልክት ለማሳየት” በሚል ሐማስ ሁለት ታጋቾችን ቢለቅም፣ የእስራኤሉ ፕሬዝደንት ቤንያሚን ነታንያሁ “ድል እከሚያደርጉ ድረስ” ለመዋጋት ዝተዋል።

ተዋጊ ጄቶች በጋዛ የሚገኙ በርካታ ኢላማዎችን መደብደባቸውን የእስራኤል ሠራዊት አስታውቋል።

ካን ዩኒስ በተባለ ስፍራ ከ24 ሌሎች ነዋሪዎች ጋር፣ በአንድ አሁን እስራኤል ባፈረሰችው ሕንጻ ውስጥ ይኖር የነበረው ኢዛልዲን አል ፋራ፣ “እኛ እስራኤልን ምን አደረግንት?” ሲል ጠይቋል።

በደቡብ የሀገሪቱ ድንበር በኩል፣ በጋዛ አዲስ ጥቃት ተፈጽሞብኛል ስትል እስራኤል አስታውቃለች፡፡ በስተሰሜን በኩል ባለችው አሽዶድ ከተማም የአደጋ ማስጠንቀቂያ ተሰምቶ እንደነበር ታውቋል። በሁለቱም ክስተቶች ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱ የተገለጸ ነገር የለም።

ትናንት ዓርብ ሐማስ ሁለት ታጋች አሜሪካውያንን ለቋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት ወቅት ከታገቱት 200 የሚሆኑ ሰዎች ውስጥ፣ ሁለቱ እናትና ልጅ አሜሪካውያን መጀመሪያ የተለቀቁ ናቸው ተብሏል።

እስራኤል ጥቃት ከጀመረች አንስቶ፣ ከ4ሺሕ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን እና ከነዚህም ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ሕፃናት እንደሚገኙበት የፍልስጤማውያኑ የጤና ሚንስቴር አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG