በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው መመለስ ያልቻሉ የዐማራ ክልል ተማሪዎች “መንግሥት ያግዘን” አሉ


ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው መመለስ ያልቻሉ የዐማራ ክልል ተማሪዎች “መንግሥት ያግዘን” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:28 0:00

በዐማራ ክልል በተስፋፋው ግጭት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በመስተጓጎሉ፣ በክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወደየሚማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መመለስ እንዳልቻሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

በሐዋሳ እና በዲላ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚማሩ የገለጹልንና ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁን ተማሪዎች፣ ከሚኖሩባቸው የክልሉ አካባቢዎች ወደ ዐዲስ አበባም ኾነ የአውሮፕላን በረራ ወዳለባቸው ከተሞች ለመሔድ እንደተቸገሩ ገልጸዋል፡፡ ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ፣ ከክልሉ ወደ ዐዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ሦስት እጥፍ በኾነ ወጪ ከክልሉ በአውሮፕላን ለመውጣት እንደተገደዱ ጠቅሰው፣ መንግሥት ወደየ ሚማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች በበኩላቸው፣ የዐማራ ክልል ተማሪዎቻቸውን በከፊል እየተቀበሉ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ፣ “ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልኹት ነው፤ ድጋፍ እና ክትትልም እያደረግኹ ነው፤” ብሏል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG