በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የሐማስን ጥቃት እንድታወግዝ እስራኤል በድጋሚ ጠየቀች


ኢትዮጵያ የሐማስን ጥቃት እንድታወግዝ እስራኤል በድጋሚ ጠየቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:13 0:00

ኢትዮጵያ፣ የሐማስን ጥቃት እንድታወግዝና ከእስራኤል ጎን እንድትቆም፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ በድጋሚ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱን፣ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው፣ በወቅታዊው የእስራኤል-ሐማስ ግጭት ዙሪያ ተወያይተዋል።

ስለ ውይይቱ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶመር ባርላቪ፣ “ሐማስ የፈጸመውን ጥቃት፣ ኢትዮጵያ በይፋ እንድታወግዝ በድጋሚ ጥሪ አቅርበናል፤” ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

ኾኖም ሚኒስቴሩ፣ በማኅበራዊ ድረ ገጹ ባጋራው መረጃ፣ “ውይይታቸው፥ ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ በማፈላለግ አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ” እንደነበር አስታውቋል፡፡ስለ ውይይቱ ዝርዝር ይዘት ግን የገለጸው ነገር የለም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG