በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጋሾች ለስደተኞች የጀመሩት ርዳታ በሦስተኛ ወገን እንደሚታደል ኢትዮጵያ አስታወቀች


ለጋሾች ለስደተኞች የጀመሩት ርዳታ በሦስተኛ ወገን እንደሚታደል ኢትዮጵያ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:52 0:00

ዓለም አቀፍ ለጋሾች፣ ለስደተኞች ዳግም የጀመሩት የርዳታ አቅርቦት፣ በሦስተኛ ወገን እንደሚታደል ኢትዮጵያ አስታወቀች።

በኢትዮጵያ ባሉ ሁሉም የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች፣ የምግብ ርዳታ ስርጭቱ እንደተጀመረ፣ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ዲሬክተር ጠይባ ሐሰን ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት(USAID) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም(WFP)፣ ለስደተኞች የሚያደርጉትን ርዳታ እንደሚጀምሩ፣ ሰሞኑን መግለጻቸው ይታወቃል።

ከለጋሾቹ ጋራ በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ ርዳታው፥ መንግሥታዊ ባልኾኑ ድርጅቶች እንዲከፋፈል እየተደረገ እንደሚገኝ፣ ወይዘሮ ጠይባ ተናግረዋል፡፡ የመንግሥት ሓላፊነትም፣ ቁጥጥር ማድረግ እንደኾነም ገልጸዋል።

በጋምቤላ በሚገኙ ሦስት መጠለያ ጣቢያዎች ብቻ፣ 30 የሚደርሱ ስደተኞች በረኀብ እንደሞቱ፣ ከዚኽ ቀደም የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለስደተኞች የሚደረገው ርዳታ መጀመሩን አረጋግጧል፡፡ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ርዳታ ማግኘት አለመቻላቸው ግን አሳሳቢ እንደኾነ አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም፣ ለሀገር ውስጥ ተረጂዎች ርዳታ አለመጀመሩን ተችቶ፣ በቅርቡ ይጀመራል ብሎ እንደሚጠብቅ ጠቁሟል፡፡

XS
SM
MD
LG